Friday, June 29, 2012

"የዋልድባን ልማት በግድም በውድም መቀበል ይኖርባችኋል" መንግስታችን


  • "እርሶ እኛን አይወክሉንም እና ልንሰማዎትም ሆነ ቡራኬዎትን አንቀበልም" ከመነኩሳት ወገን      ለብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ
  • "በዋልድባ ገዳም ምንም ድርድር አናደርግምየአካባቢው ነዋሪ
  • በርካታ ወጣቶችም በመንግሥት ታጣቂዎች ታፍሰው ተወስደዋል
ባለፈው ቅዳሜ በዓዲርቃይ ከተማ ላይ በዋልድባ አካባቢ ሊሰራ በታቀደው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ዙሪያ የአካቢው ነዋሪዎችን፣ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኤልሳዕ በተገኙበት፣ የመንግሥት ተወካዮች፣ የማኅበረ መነኩሳቱ ተወካዮች በተገኙበት እንዲሁም ከቤተክህነት ተወካዮች በተገኙበት የማስፈራራቱ እና በግድ የማሳመኑ ስራ እንደቀጠለ ነው። ሰሞኑን በደረሱን መረጃ መሰረት መንግስት ለልማቱ እፈልጋቸዋለው ከሚላቸው የዋልድባ ገዳም ክልል ውስጥ የሚፈርሱን መካናት የሚከተሉት ናቸው፡

  • ከአበረንታት
    • ማርገፅ ቅዱስ ሚካኤል  ቤተክርስቲያን
    • ድል ሰቆቃ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን
    • እጣኑ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም  ቤተክርስቲያን
    • ሙሉ ቤት ቅዱስ ሚካኤል  ቤተክርስቲያን
  • ከአባ ነፃ
    • ዲዋር ግዛ ቅዱስ ተክለሃይማኖት  ቤተክርስቲያን
    • ማይ ሸረፋ አቡነ አረጋዊ  ቤተክርስቲያን
    • አዲ ፈረጅ አብዮ እግዚ  ቤተክርስቲያን
    • ማይ ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ቤተክርስቲያን
    • ታች እጣኖ ቅዱስተ ማርያም  ቤተክርስቲያን
    • ላይ ኩርማ አቡነ አረጋዊ  ቤተክርስቲያን
    • ጎድጓድ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ቤተክርስቲያን
    • ቃሊማ አቡነ ሳሙኤል  ቤተክርስቲያን
    • ቃሊማ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን
    • ቃሊማ ቅድስት ሥላሴ  ቤተክርስቲያን
    • ማይ ዓርቃይ ቅዱስ ሚካኤል  ቤተክርስቲያን እና ሌሎችም ስማቸው ያልተገለጸ አብያተ ክርስቲያናት እንደሚነሱ ዘገባው ደርሶናል።

በባቦጋያ መድሃኒአለም የቦታ ጉዳይ 13 ሰዎች ላይ እያንዳንዳቸው ሰባት ወር ተፈረደባቸው


  • ከ400 በላይ ምዕመናን በእንባ ወደ እስር ቤት ሸኝተዋቸዋል፡፡
  • የፍርድ ቤቱ ውሳኔ የበላይ አካል ተጽህኖ አለበት ፤

(አንድ አድርገን ሰኔ 22 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በፍርድ ቤቱ ውሳኔ በጣም አዝነናል ፤ ሲጀመር አንስቶ በባቦጋያ መድሃኒዓለም ቦታ እና በኩሪፍቱ ሪዞርት መካከል ያለው የቦታ ውዝግብ በየጊዜው ማቅረባችን ይታወቃል፤ አቅማችን በፈቀደው መጠን ጉዳዩን ሰዎች ዘንድ እንዲደርስ የመፍትሄ አካላት እንዲሆኑ ያላሰለሰ ጥረት አድርገናል ፤ ከወራት በፊት የቤተክርስትያኑን ቦታ በአካባቢው ምዕመናን ጉዳዩን ዳር እዲያደርሱ የተወከሉ ሰዎች በፍርድ ቤት “እናንተ መጠየቅ አትችሉም ቤተክርስትያኒቱ የወከለቻችሁ አካላት አይደላችሁም” በማለት ለኩሪፍቱ ሪዞርት ባለቤት እንደተወሰነለት ገልጸን ፅፈን ነበር ፤ 

Thursday, June 28, 2012

እባካችሁ ተፋቱልን



by Birhanu Admass Anleye (ከፌስ ቡክ ላይ የተወሰደ)
  ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ሃይማኖት ዐምድ ‹‹ ፖለቲካና ሃይማኖት›› በሚለዉ ርእሰ ጉዳይ ከተስተናገደ በኋላ በመጽሔቱ የቦታ ዉስንነት ምክንያት የቀነስኳቸዉን ሁለት አንቀጾች በማካተት የቀረበ ነዉ፤ መልካም ንባብ፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዐቢይ ጾም የሚዉሉት እሑዶች እያንዳንዳቸዉ አንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ተአምርን የሚያስታዉስ ስም አላቸዉ፡፡ ለምናገረዉ ታሪክ መነሻ የሆነዉ አራተኛዉ እሑድም መጻጉዕ ይባላል፡፡ በዚህም ጌታችን በምድር ላይ በሽተኞችን የፈወሰበት ተአምራት፣ 38 ዓመት ያህል አንድ አልጋ ላይ ተኝቶ መዳኑን ሲጠባበቅ ከኖረ በኋላ በጌታ በተፈወሰዉና በተለምዶ ‹‹ መጻጉዕ›› (በሽተኛዉ ማለት ነዉ እንጂ የመጠሪያ ስም አልነበረምእየተባለ በሚጠራዉ ሰዉ ታሪክ መነሻነት ይታሰባል፡፡ በወንጌል እንደተጻፈዉ ጌታ ወደ በሽተኛዉ ከደረሰ በኋላ አስቀድሞ ልትድን ትወዳለህን ሲል ጠየቀዉ፡፡ መልሱን ከሰማ በኋላም ‹‹ ተነሣ አልጋህን ተሸክመህ ሒድ›› ሲል አዘዘዉና  በሽተኛ ወዲያዉ ተነሥቶ ድኖ አልጋዉን ተሸክሞ ሔደ፡፡ ታዲያ በዐብዮቱ ዋዜማ አካባቢ በነበረዉ የመጻጉዕ እሑድ እንዲህ ሆነ ይባላል /ዮሐ 51-10/ ፡፡ በዕለቱ ንጉሡም በተገኙበት ቅዳሴዉ ከተቀደሰ በኋላ በተነበበዉ ወንጌል ላይ የሚያስተምሩት እስካሁን የሊቅነትና የእዉነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ስብከት መለኪያ ተደርገዉ ከሚጠቀሱት እጂግ በጣም ጥቂት የሀገራችን ሊቃዉንት አንዱ የነበሩት  መልአከ ሰላም ሳሙኤል ተረፈ ‹‹ተንሥእ ወንሣእ ዐራተከ  ወሑር፤  ተነሥ አልጋህን ተሸክመህ ሒድ›› በሚለዉ ኃይለ ቃል መነሻነት ትምህርቱን ይሰጣሉ፡፡ በጊዜዉ ነበርን፤ የተደረገዉን አይተናል ሰምተናል የሚሉ ሰዎች እንደ ነገሩኝ ንጉሡ በዚህ ትምህርት በጣም ተበሳጭተዉ ነበር፡፡ ምክንያቱም ‹‹ አልጋህን ተሸክመህ ተነሥና ሂድ›› የሚለኝ እኔን ነዉ ብለዉ በጊዜዉ ከነበረዉ የሶሻሊስት ርእዮተ ዓለም አራማጅ የተማሪዎች እንቅስቃሴዎች ጋር አገናኝተዉ ስለተመለከቱት የተሰበከዉ በሙሉ ወንጌል ሳይሆን አዲሱ ፖለቲካ መስሏቸዉ ነበር ይባላል፡፡ መልአከ ሰላም ሳሙኤልም ብዙ ሳይቆዩ ስለሞቱ ለአንዳንድ ሰዎች  ትምህርቱን ለሞታቸዉ ምክንያት አድርገዉ እንዲናገሩ ምክንያት ሆኗቸዋል፡፡

Wednesday, June 27, 2012

1061 የሃይማኖት ድርጅቶች የመቋቋሚያ ፍቃድ ጠይቀዋል


ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበብ


(አንድ አድርገን ሰኔ 20 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የፌደራል ጉዳዮች  ሪፖርት በቅርቡ አንድ ሰው አምጥቶልን ማንበብ ችለን ነበር  ፤ ሪፖርቱ ከሃይማኖት ጽንፈኝነት ፤በሀገሪቱ ላይ በሃይማኖቶች መካከል የተከሰተውን ችግርን እንዴት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ እንደፈታው የሚያትት ጉዳይ ይገኝበታል ፤ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግቢ ተማሪዎች ሃይማኖታዊ በዓል ለማክበር በጠየቁበት ጊዜ ያቀረቡት ጥያቄ አግባብ አለመሆኑን ከሚመለከታቸው የሃይማኖት አባቶች ጋር በመወያየት የበዓል አከባባሩ ከግቢ ውጪ መሆን እንዳለበትና በጊዜው በዓሉን በዩንቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳልተከበረ ያስቀምጣል ፤ በመቀጠልም በጅማ አካባቢ የተከሰተውን ችግር ለመፍታት ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ለአካባቢው ነዋሪዎች በርካታ ስልጠናዎችን እንደሰጠ እና ከ7000 በላይ ጽሁፎችን ከበርካታ ለማህበረሰቡ እንዳሰራጨ ይናገራል ፤ በአሁኑ ሰዓት ከየሃይማኖት ተቋማቱ በማሰባሰብ የሃይማኖት አንድነት ጉባኤ በየጊዜው መደረጉ በአሁኑ ሰዓት የሚታዩ ችግሮችን ከመፍታትና መስመር ከማስያዝ አኳያ መስሪያ ቤቱ በዚህ ላይ ትልቅ ስራ እንደሰራ አስፍሯል፤ በተጨማሪም በጥምቀት በዓል ወቅት የሃይማኖትን እኩልነት በሚጻረር መልኩ አንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኞች በቲሸርቶቻቸው ላይ ያሰፈሯቸው ጽሁፎች እንደ አንድ ችግር በማንሳት በዚህ ላይ የሚመለከተው አካል ሁሉ ህገ መንግስቱን ከማስከበር እና የሃይማኖት እኩልነትን ከማረጋገጥ አኳያ አብሮ መስራት እንዳለበት ያትታል፡፡

Tuesday, June 26, 2012

የቁጥር ነገር


ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበብ

(አንድ አድርገን ሰኔ 19 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በርካታ ጊዜያት መንግስት እና አለማቀፋዊ ተቋማት የቁጥር ነገር አያስማማቸውም ፤ IMF ወይንም World Bank የሀገሪቱ እድገት በዚህኛው ዓመት 6 ከመቶ አይበልጥም ብሎ ሲተነብይ መንግስት ደግሞ “አይሆንም እኛ ለተከታታይ 6 ዓመታት 11.2 በመቶ ነው ያደግነው” በማለት ዓመታዊ ያልተሰላ ሂሳብ ያቀርባል እና በየዓመቱ ሰኔ አልፎ ሀምሌ ሲመጣ የቁጥር ነገር ዋናው የመከራከሪያ ያለመስማሚያ ነጥብ ሆኖ መመልከት የዘወትር ተግባራችን ከሆነ ሰንበትበት ብሏል፡፡ አሁን እኛ አነሳሳችን ስለ እንደዚህ ዓይነት ነገር ለመናገር አይደለም  ፤ ባይሆን ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ ይህ “የቁጥር ነገር” በሙስሊም ወንድሞቻን ዘንድ እንዴት እየቀረበ መሆኑን ለማስገንዘብ እና ለማሳየት በማሰብ ነው “የቁጥር ነገር” በማለት የተነሳነው፡፡

Monday, June 25, 2012

የአዲስ ራዕይን ጽሁፍ በPdf ያንብቡ


(አንድ አድርገን ሰኔ 18 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- “አዲስ ራእይ” ላይ የሰፈረውን ጽሁፍ በሁለት ክፍል ማስቃኝታችን ይታወቃል ፤ ጽሁፉን ወደ ፒዲፌ ቀይረን ለአንባቢያን ለማቅረብ ቃል በገባነው መሰረት ሙሉ ጽሁፉን ማንበብ የምትፈልጉ ሰዎች የሚቀጥሉትን ሊንኮች በመጠቀም ሙሉውን ጽሁፍ ማንበብ የምትችሉ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ እኛ ጽሁፉን ያየንበትን እይታ ለማቅረብ ሞክረናል እስኪ እርስዎም ይዩትና ያዩበትን እይታ ይጻፉልን ፤ ጽሁፉ ምን አይነት አላማን አንግቶ ነው የተጻፈው ? ምንስ ተጽህኖ ወደፊት ያሳድራል ? መንግስት ምን እያሰበ ይመስሎታል ? መሰል ነገሮችን በራስዎ እይታ አይተው ሀሳብዎን ያካፍሉን….

Sunday, June 24, 2012

የእመቤታችን ተዓምር

(አንድ አድርገን ሰኔ 18 2004 ዓ.ም)፡- ቀኑ እለተ ሰንበት ሰኔ 17 2004 ዓ.ም  ፤ ሰንበት እንደመሆኑ የት ሄጄ እንደማስቀድስ ሳወጣ ሳወርድ ውስጤ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያር ገዳም ቤተክርስትያን እንድሄድ  አመላከተኝ ፤ ቦታው ጦር ኃይሎች ወደ ወይራ-ቤተል ሲሄዱ አጉስታ ልብስ ስፌት ፋብሪካ አለፍ ብሎ የምትገኝ ቤተክርስትያን ናት ፤ በጣም በጠዋት በመነሳት ካህናት ቅዳሴ ሳይገቡ ለመድረስ ተጣደፍኩኝ ፤ እንደ ሃሳቤም ተሳቶልኝ ቅዳሴ ሳይገቡ መድስረስ ቻልኩኝ ፤ ቅዳሴው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ደስ በሚያሰኝ እኛ ውስጥን ሀሴት በሚሞላ መልኩ ቅዳሴው ተጠናቀቀ ፡፡ ከዚያ ቅዳሴው ከተጠናቀቀ በኋላ የቀኑ ተዓምረ ማርያም ተነበበ ፤ ምዕመኑ ሁሉ ቆሞ ፍጹም በሆነ ፀጥታ የእመቤታችንን ተዓምር አደመጠ፡፡

Friday, June 22, 2012

የ“አዲስ ራዕይ” አመለካከት (ክፍል 2) ….



ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበብ

  •  ዋህቢያ ይሁን ከማህበረ ቅዱሳን ወይም ከሌላው እምነት ውስጥ ጽንፈኝነት አይመለከተኝም የሚለው በግላጭ ወጥቶ እንዲያወግዝ እድል ሊኖረው ይገባል
  •  ኢህአዴግ የቄሱም የሼሁም ድርጅት ነው ፡፡ ከአባልነት አንጻር የየትኛውም እምነት ተከታይ መሆን ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም ፡፡ የአንድ እምነት ሰባኪ  የሆነ ሰው ኢህአዴግ አባል መሆን ይችላል  የኢህአዴግ አመራር መሆንን ግን አይፈቀድም
  • ደርግ ግለሰቦችን በተናጠል  ሲገድል እናንተ ደግሞ ገዳማትን በማፍረስ በጅምላ እምነትንና አማኞችን  የመግደል ምግባር ላይ ተሰማርታችኋል
  • በርካታ አባላት ማህበረ ቅዱሳን እንደሆኑት ሁሉ በርካታ አባላትም የወሃቢያ ወይ  የሌላ የእስልምና ፈለግ ተከታዮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ችግሩ የትኛውም እምነት ይከተሉ የሚለው አይደለም ፡፡ ችግሩ ያለው..............................

(አንድ አድርገን ሰኔ 15 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ከትላንት በስተያ በወፍ በረር በመቃኝት “አዲስ ራዕይ” መጽሄትን በጥቂቱ ለማስዳሰስ ሞክረን ነበረ ፤ አሁን ደግሞ  ምን አይነት ነጥቦች እንዳካተተ ፤ በየነጥቦቹ ስር ምን ዓይነት ሀሳቦችን እንደሚያነሳ ለማሳየት እንሞክራለን ፤ የአጻጻፍ ይዘት እና የጽሁፉን ፍሰት አብረን እንቃኛለን፡፡ የራሳችንንም ሃሳብ ጣል በማድረግም እናያለን ፤ ፅሁፉ ሲጀምር “በሰላምና ህገ-መንግስቱ ዙሪያ ሀገራዊ መግባባት መፍጠር የዜጎችና የመንግስት መብትም ግዴታም ነው” በማለት  ይጀምራል፡፡

“አንድ አድርገን” ለሁለተኛ ጊዜ ተዘጋች



ኢትዮጵያ ውስጥ ብሎጋችንን ለማንበብ www.andadirgen.blogspot.ca ይጠቀሙ
  •  “ጠላት የዘጋውን በር አትመልከት ፤ እግዚአብሔር እጅ ያለውን ቁልፍ ተመልከት”  አቡነ ሺኖዳ

(አንድ አድርገን ሰኔ 15 2004 ዓ.ም)፡-ህገ መንግስታችን አንቀጽ 29 ቁጥር 1 ላይ “ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት ለመያዝ ይችላል” ይላል አንቀጽ ቁጥር 2 ደግሞ “ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው ፡፡ ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሁፍ ወይም በህትመት በስነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም ማሰራጫ ዘዴ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሀሳብ የመሰብሰብ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል” በማለት ያስቀምጣል ፤

Tuesday, June 19, 2012

ኢህአዴግ “በአዲስ ራእይ” መጽሄት ምን እያለ ነው?


  • በተመሳሳይ አንዳንድ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ሌላው ቀርቶ የተለየ አመለካከት ያላቸው ክርስትያኖችንም ቢሆን የሚከተሉትን እምነት ክርስትና አይደለም ብለው ከማመን አልፈው ፤ እነዚህ ተለየ አመለካከት ያላቸው ዜጎች እምነታቸውን በነጻነት እንዳያራምዱ በተለያየ ሽፋን ማፈን ይከጅላቸዋል፡፡
  • ኢትዮጵያ የክርስትያነ ደሴት ናት ከሚል ቅዥት ባለፈ አንድ “ሀገር አንድ ሃይማኖት” የሚል መፈክር ደረታቸው ላይ ለጥፈው ለመሄድ እንኳን ሀፍረት የማይሰማቸው ሆነው በአደባባይ ይታያሉ
  • ወሃቢያን ወይም ሌላው የመከተል የማህበረ ቅዱሳንን ወይም ሌላ አተያይ የመያዝ መብት የዜጎች ነው 
  • ህዝብ እንዲያገለግል የተቀመጠ ኃላፊና ሰራተኛ በራሱ እምነት ምስሎች አጨመላልቆ የምናይበት ሁኔታ መንግስትና ሃይማኖትን ለመለየት የተቀመጠውን ድንጋጌ በቀጥታ በመጻረር በመሆኑ መወገዝ መወገድ የሚገባው ነው፡
  • በክርስትና ውስጥም በአንድ ወይም በሌላ መልኩ በተለይ ከማህበረ ቅዱሳንም የተወሰኑ ከመሰረታዊ የእምነቱ አስተምህሮ ፈንጠር ያሉ .........
  • እነዚህ ፅንፈኞች በርካታ ንጹሀን ዜጎችን አሳስተው በማነሳሳትና አንዱ በሌላው  ለመዝመት የተዘጋጁ በማስመሰል የፍጥጫ ድባብ እንዲነግስ የሚሰሩ ናቸው

(አንድ አድርገን ሰኔ 12 /2004ዓ.ም)፡-PART 1
አዲስ ራዕይ በየሁለት ወሩ በአማርኛ ቋንቋ እየተዘጋጀች በኢኮኖሚያዊ ፤ ፖለቲካዊ ፤ ማህበራዊ ፤ ዓለም ዓቀፋዊና ፤ ድርጅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራያና ትንታኔ ይዛ የምትቀርብ የኢህአዴግ የትንታኔ መጽሄት ነች፡፡ የዚች መጽሄት አዘጋጅ “የኢህአዴግ ህዝብ ግንኙነት ክፍል” ሲሆን አሳታሚው ደግሞ “ኢህአዴግ” መሆኑን የመጽሄቷ የፊት ገጽ ላይ የሰፈረው ጽሁፍ ይናገራል ፡፡

Monday, June 18, 2012

ቅ/ሲኖዶስ በተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅነት ያወገዛቸው 7 ድርጅቶችና 16 ግለሰቦች ውሳኔ ለአህጉረ ስብከት ተሰራጨ


·         መናፍቃ በማንኛውም የቤተ ክርስቲያናችን የክህነት፣ የክብርና የማዕርግ ስም አይጠሩም
·         የቤተ ክርስቲያኒቱን የከበረ ስሟን በማጉደፍ ታሪኳንና ክብሯን በመዳፈራቸው በሕግ ይጠየቃሉ
·         መናፍቃ እና ድርጅቶቹ ላሰራጯቸው ኅትመቶች የማስተባበያ ጽሑፎች ይዘጋጃሉ
·         ሊቃውንት ጉባኤ ከማንኛውም አካል ለሚሰነዘረው ሃይማኖት የሚያጎድፍ ክብረ ነክ ጽሑፍ ምላሽ ለመስጠት በሚችልበት አኳኋን በጥራትና በስፋት ይጠናከራል
·         ከተወገዙት ድርጅቶች መካከል የ”አንቀጸ ብርሃን” ድርጅት መሥራች በኾነውና በእጅጋየሁ በየነ አቅራቢነት የፓትርያኩ መልእክቶች ጸሐፊ እስከመኾን ደርሶ በነበረው አሸናፊ መኰንን ላይ የተላለፈውን የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ ለመቀሠጥ የተደረገው የሸፋጮች ሙከራ ከሽፏል (ሙከራውን የሰነዱን ገጽ 38 እና 39፣ ተ.ቁ 16ን በማነጻጸር ይመልከቱ)
·         “አሁን የተሐድሶ መናፍቃኑ ዝናራቸውን ጨርሰው የአገልጋዮችን ስም ማጥፋቱን ተያይዘውታል፤ ያወገዝናቸው ስለጠላናቸው ሳይሆን ስለካዱ ነው፤ ሰውን ማስታመም የሚቻለው በምግባር ድክመቱ እንጂ በሃይማኖት ክሕደት አይደለምና፡፡” /ብፁዕ አቡነ አብርሃም የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ለሀ/ስብከታቸው ሰባክያነ ወንጌል እና ምእመናን ይፋ ሲያደርጉ ከተናገሩት/
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 9/2004 ዓ.ም፤ ጁን 16/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለቤተ ክርስቲያንና ለሃይማኖት ጉዳይ በተለይም ለምእመናን አንድነት ቅድሚያ በመስጠት፣ በጉዳዩ ላይ በስፋት በመነጋገር፣ ግንቦት 15 ቀን 2004 ዓ.ም፣ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ድርጅቶች፣ ግለሰቦች እና መጽሐፎቻቸው ላይ በአንድ ድምፅ ያስተላለፈውን የውግዘት ውሳኔ የያዘው ቃለ ጉባኤ ለመላው አህጉረ ስብከት ተሰራጨ፡፡
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሰኔ 7 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ 48 አህጉረ ስብከት ባሰራጨው ቃለ ውግዘት የተካተቱት መናፍቃን ድርጅቶች ሰባት ሲኾኑ የግለሰቦቹ ብዛት ደግሞ 16 ነው፡፡